ትርጉም ያለውና የተሟላ ሕይወት እንድንኖር ጥሩና መጥፎን መለየትና በነዚህ መርሆችና/ሕግጋቶች አክብሮ መኖርን የመሰለ መንገድ የለም። የሰው ልጅ ጥሩና መጥፎን ለመለየት የተለያዩ መንገዶችን ይጠቀማል፤ ከንዚህም ውስጥ ቤተሰብ፣ ሀይማኖት፣ ማህበረሰብ እና ሕሊናችን ዋናዎቹ ናቸው።
እነዚህን የመርህ በቀላሉ መሸርሸር ችግር ያየው ኒቻ (Nietzsche) Morality በአንዴ የምንቀበለው ነገር ሳይሆን በየቀኑ መፈተሽ አለባት የኑሮ ዘዴ ናት ሲል በተለያዩ ጹሑፎቹ ላይ ያስተማረው። ከዚህም አልፎ ኒቻ የሐይማኖቶችን መርህ ቀጥታ ከመከተል የሰውን ልጅ የግሉንና የማሕበረሰቡን Value መፈተሽና መመርመር ይገባዋል ብሎ ያስባል።
ለምሳሌ ኒቻ ሃይማኖታዊ ተቋማትና ቀደምት ፈላስፎች በሙላ የሚሰብኳቸውን እራስን ዝቅ ከማድረግ ጋር የሚገናኙ የሚከተሉትን መርሖች በጥብ ይቃወማል
ኒቻ በተቃራኒው ሕይወትን የሚያፋፉ የሚላቸወን መርሆች ዘርዝሯል
ጥሩና መጥፎ
ጥሩና መጥፎን ለመለየት የምንከተለው ሃይማኖት ከፍተኛ የሆነ እገዛ የሚያደርግልን ሲሆን። ጥሩና መጥፎን ለይተን ስንኖር ግን ሃጂ የይም ቄሱ ስላሉ ብቻ ከሆነ የእምነታችን ጥንካሬ ጊዜያዊና ከላይ ከላይ ብቻ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ ስላለ ወይም ገሃነም ላለመግባትም የምንከተላቸው መርሆች ሲፈተኑ በቀላሉ ይፍረከረካሉ። ብዙ የሀይማኖት አባቶች የቤተክርስትያን ንብረት የሚዘርፉትም ለዚሕ ነው። ጥሩ ሀይማኖተኛም ሰው ስልጣን ላይ ሲወጣ ያደገበትን መርሕ ረስቶ "ሲሾም ያልበላ... " የሚለው ለዚሁ ነው።እነዚህን የመርህ በቀላሉ መሸርሸር ችግር ያየው ኒቻ (Nietzsche) Morality በአንዴ የምንቀበለው ነገር ሳይሆን በየቀኑ መፈተሽ አለባት የኑሮ ዘዴ ናት ሲል በተለያዩ ጹሑፎቹ ላይ ያስተማረው። ከዚህም አልፎ ኒቻ የሐይማኖቶችን መርህ ቀጥታ ከመከተል የሰውን ልጅ የግሉንና የማሕበረሰቡን Value መፈተሽና መመርመር ይገባዋል ብሎ ያስባል።
ለምሳሌ ኒቻ ሃይማኖታዊ ተቋማትና ቀደምት ፈላስፎች በሙላ የሚሰብኳቸውን እራስን ዝቅ ከማድረግ ጋር የሚገናኙ የሚከተሉትን መርሖች በጥብ ይቃወማል
- እኩልነት (Equality) - የሰው ልጆች እውነት እኩል ነን? እኩልነትስ ጥሩ ነገር ናት?
- ሀዘኔታ (Compassion) - ለደካሞች ማዘን ደካሞችን ያበረታቸዋል ወይስ የባስ ያዳክማቸዋል? ለማሕበረሰባችንስ ምን ፋይዳ አለው?
- መስዋትነት (Self-sacrifice) - እራስን ለተለያዩ አላማዎች ለምሳሌ ለሐገር መሰዋእትነት?
እነዚህን መርሖች ኒቻ ሕይወትን የሚያቀጭጩ፣ ሓያልነትን የሚያስቀሩና ለእድገት ያማያዋጡ ይላቸዋል። ብናልባት ዲሞክራቲክ ሶሳይቲ ለመመስረት ይጠቅሙን ይሆናል እንጂ የግል ብቃትን አያበረታቱም፣ ታላቅነትን አያነቃቁም ለሕይወት ትርጉምና ጥሩነት በንገድ አይዎኑም። እነዚህ መርሆች የሚጥሩት የራስን ሕይወት ጥሩ ለማድረግ ሳይሆን የሁሉንም ሰው ጥሩ ለማድረግ ነው። የግል ሕይወታችን ጥሩ ሳይሆን ደሞ የጋራ ሕይወታችን በፍጹም ጥሩ አይሆንም።
ኒቻ በተቃራኒው ሕይወትን የሚያፋፉ የሚላቸወን መርሆች ዘርዝሯል
- ብቃት/ክህሎት (Excellence) - የሰው ልጅ እኩል ለመሆን ሳይሆን ከሁሉም የተለየ መሆኑን ተቀብሎ ሲጣጣር ብቃት ይመጣል
- የግል እድገት (Individual Development) - ሁላችንም የራሳችን መንገድ ያለን ሲሆን ይህን መንገድ ስንከተል ደካማ በማሕላችን አይኖርም ማዘንም አይጠበቅብንም
- Nobility - በማህበረሰባችን መደነቅ መሞገስ እና አንደ ሃያል መታየት የታላቅነት መንገድ ይሆን?
እነዚህ መርሆች ሕይወትን የሚያፋፉና ለረጅም ግዚ መፍትሔ የሚሆኑ ይላቸዋል።
ስቃይ እና ትግል
ከነዚህ መርሆች ጋር አብሮ ስቃይ እና ትግል ሊመጣ ይፍል ይሆናል፣ ነግር ግን ስቃይና ትግል ታላቅ ያረጉናል እንጂ ፈጽሞ አያዳክሙንም።
እነዚህን መርሆች ኒቻ በ19470ዎቹ ቢያስቀምጣቸውም የሰው ልጅ ከረጅም ውጣ ውረድ ብኋላ በራሱ መንገድ የደረሰበት ይመስላል። ምክኒያቱም በዚህ የካፒታሊዝም ዘመን የሰው ልጅ ከመቼዎም ግዜ በላይ የራሱን መርህ መከተልን እየመረጠ መጥቷል። ከዚያም አልፎ በተለያዩ ሶሻል ሚዲያ እንደምናየው ከምንም በላይ የሰውን ልጅ የሚያስደስቱት ብቃትና፣ የግል እድገት፣ መደነቅ ሆነዋል። ኒቻን እየተቃወምነው እየፈራነው እሱ ያለውን እየኖርን ይሆን እንዴ? ወይስ የቀረ ነገር አለ?
አሞር ፋቲ (Amor Fati)
ኒቻ ከላይ የዘረዘራቸውን መርሆች አስቀምጦ አላበቃም ምክንያቱም እነዚህን መርሆች ተከትላቹ ኑሩና ጥሩ ህይወት ትኖራላቹ ካለ ከላይ የተነሳበትን ዋና በርህ ሊጣሪስ ስለሆነ። በመሆኑም ኒቻ ጥሩ ኑሮ ለመኖር ሁሌም ህይወትህን መርምር፣ በየሰአቱ፣ በየቀኑ፣ በየሳምንቱ፣ በየወሩ... ህይወትህንም ስትመረምር አሞር ፋቲን ብቻ አትርሳ። አሞር ፋቲ = የእጣ ፋንታ መቀበል። የሰው ልጅ ህይወቱን ሲመረምርና ሁሉንም ስቃዩን ትግሉን ስኬቱን ሲያስተውል ከሱ ቁጥጥር ውጪ ያሉትን እጣ ፋንታዎቹን በፍቅር ሊቀበላቸው ይገባል።
አሞር ፋቲን ስንከተል እርሀብ ብርታት ይሆናል፣ አለመማር ብርሃን ይሆናል፣ በሽታ እድል ያመጣል። እራሱ ኒቼ እንዳለው የማይገድልህ ነገር ሁላ ታላቅ ያደርግሃል "What doesn't kill you makes you stronger" ይህ እንዲሆን ግን እጣ ፈንታህን ፈገግ ብለፍ መቀበልና ማስተናገድን የመሰለ ድንቅ ነገር የለም.
ለማጠቃለል ያህል ኒቻ በጣም አወዛጋቢ ፈላስፈ ነበር፣ እዚህ የተጠቀሱትን ሀሳቦች ላንቀበላቸው እንችል ይሆናል። ነገር ግን ጥሩ ኑሮ ብሎ ያስቀመጠውን የህይወት ምርመራ እና የእጣ ፈንታ መርህ ብንከተል ጥሩና ትግጉም ያለው ሕይወት የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም።
ታላቅነት = የህወት ምርመራ + አሞር ፋቲ
አሞር ፋቲን ስንከተል እርሀብ ብርታት ይሆናል፣ አለመማር ብርሃን ይሆናል፣ በሽታ እድል ያመጣል። እራሱ ኒቼ እንዳለው የማይገድልህ ነገር ሁላ ታላቅ ያደርግሃል "What doesn't kill you makes you stronger" ይህ እንዲሆን ግን እጣ ፈንታህን ፈገግ ብለፍ መቀበልና ማስተናገድን የመሰለ ድንቅ ነገር የለም.
ለማጠቃለል ያህል ኒቻ በጣም አወዛጋቢ ፈላስፈ ነበር፣ እዚህ የተጠቀሱትን ሀሳቦች ላንቀበላቸው እንችል ይሆናል። ነገር ግን ጥሩ ኑሮ ብሎ ያስቀመጠውን የህይወት ምርመራ እና የእጣ ፈንታ መርህ ብንከተል ጥሩና ትግጉም ያለው ሕይወት የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም።